Search

"‘ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ’ መፅሐፍ ለሀገራዊ ዴሞክራሲ ግንባታ ቁልፍ ሚና ይጫወታል"

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 52

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ተጽፎ ለአንባብያን የደረሰው መፅሐፍ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

መፅሐፉን በተመለከተ በተለያዩ የሥራ መስኮች የሚገኙ ባለሙያዎች እና ባለስልጣናት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተመራው መድረክ መፅሐፉ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ያለው አስተዋፅዖ በስፋት ተዳሷል።

በመድረኩ ሀሳባቸውን ያካፈሉት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፥ መፅሐፉ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ እርሾ የሚሆን የዳበረ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ እሴት እንዳላት የታየበት ነው ብለዋል።

ሌላው በውይይቱ የተሳተፉት አንጋፋው ፖለቲከኛ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በሰጡት አስተያየት፥ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ የሕዝብ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሲነሳ ከሀገረ መንግሥቱ ጋር ተጣምሮ የሚነሳ በመሆኑ የዴሞክራሲ ግንባታ ጉዞውን እንዳወሳሰበው ገልፀዋል።

መፅሐፉ ይህን የዘመናት የዴሞክራሲ ጥያቄ ከኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ጋር አገናኝቶ ማምጣቱ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በመሰለች ጥንታዊት እና የዳበረ ባህላዊ ሥርዓት ባላት ሀገር ዴሞክራሲን መገንባትን እንቆቅልሽ ያደረገው ምስጢር እንቅልፍ እንደሚነሳቸው የተናገሩት ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፤ ይህ ቁጭት “ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ” የሚለውን መፅሐፍ እንዲጽፉ እንዳነሳሳቸው ገልፀዋል።

መፅሐፋ ወደፊት ለኢትዮጵያ የሚበጅ ዴሞክራሲን በመገንባት ሂደት መነሻ ሀሳብ ሆኖ እንደሚያገለግል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

#ኢቢሲዶትስትሪም #ተስፋዬበልጅጌ(/) #ኢትዮጵያዊዴሞክራሲፍለጋ