የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አምስት ዓመታት የነዋሪዎችን መሠረታዊ ፍላጎት እና አንገብጋቢ የሆነውን የቤት ችግር በመረዳት አዲስ የለውጥ እሳቤን እውን በማድረግ 496 ሺህ 971 ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች እንዲተላለፉ ማድረጉን አስታውቋል።
ከተማ አስተዳደሩ በቤት ግንባታ ልማት ሂደት ውስጥ የመንግሥት ሚና ቀዳሚ በማድረግ የተለያዩ የግንባታ አማራጮችን በመዘርጋት ቤት አልሚ ሪል እስቴቶች፣ የግል አልሚዎች ሕብረት ሥራ ማህበራት እና በጎ ፈቃደኞች ተቀናጅተው በመኖሪያ ቤት ልማት ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን አመልክቷል፡፡
በተለይም ከተማ አስተዳደሩ የአጭር ጊዜ እቅዶችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ ሥራዎችን በመተግበር ላይ ሲሆን፣ በተጨማሪ በዘንድሮው ሩብ ዓመት ብቻ የመርካቶ በጎነት መንደርን ጨምሮ ከ4 ሺህ 200 በላይ ቤቶች በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
እነዚህ የቤት ግንባታዎች ንጹህ የመኖሪያ አካባቢን የፈጠሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ምቹ አካባቢ በመፍጠር የልጆች መጫወቻ የተሰራላቸው ሰው የሚንቀሳቅስባቸው አና የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከሪያ ስፍራ የተሟላላቸው የዜጎችን ክብር የሚመጥኑ መኖሪያ መንደሮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በአጠቃይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ተነሺዎችን፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን፣ አረጋውያንንና የሀገር ባለውለታዎችንና ሌሎች ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል አካታች የሆነ የልማት ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: