የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት፣ በሩብ ዓመቱ በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር የተከናወኑ ሥራዎች አበራታች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በክልሉ እስከ አንደኛው ሩብ ዓመት 1 ሚሊዮን 941 ሺህ 842 ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡
የመደመር መንግሥት የኢኮኖሚ ምሰሶ አድርጎ እየሠራ የሚገኘው የማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻል እየታየበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ዘርፉን በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ እንዳይፈጥር መሥራት ይጠበቃል ብለዋል።
በሩብ ዓመቱ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ልዩ አነስተኛ፣ ባህላዊ እና የወርቅ አምራች ኩባንያዎች አማካይነት ወደ ብሔራዊ ባንክ ከ3 ሺህ 800 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ገልጸዋል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ሺህ 709 ኪሎ ግራም ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ አበራታች ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በክልሉ የሚገኙ ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።
በነስረዲን ሀሚድ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: