Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞስኮ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ነጥቦች፦

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 59

በሞስኮ በሚካሄደው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የጋራ ቁርጠኝነት እና ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላቂ ብልጽግናዋ እና ለሀገራዊ እድገቷ መሰረት በሆኑ ሦስት ቁልፍ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች፦ በምግብ ዋስትና፣ በአስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እና በዕውቀት ሽግግር።

የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ፣ በመከባበር እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የጸና ታሪካዊ ወዳጅነት ነው።

ከሩሲያ ጋር በጋራ በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን በቁርጠኝነት እያከናወንን እንገኛለን፤ ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የብልጽግና ጉዟችንን በእጅጉ የሚያፋጥን ነው።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: