Search

ኢትዮጵያ በድርድር የሚመጡ መፍትሔዎችን እና በአፍሪካ የሚመሩ የሽምግልና ሂደቶችን ትደግፋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 69

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም የሩሲያ ኩባንያዎች የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚፈጥረውን ዕድል በመጠቀም በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣናዎች ውስጥ በመድኃኒት ማምረቻ እና በማሽነሪ ዘርፎች የጋራ ሽርክናዎችን በመመሥረት ለአፍሪካ ገበያ ምርት ማቅረብ እንደሚችሉ አመልክተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚኖሩ የክፍያ ሥርዓቶችን ማቀላጠፍም የንግድ ወጪን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረገድ ኢትዮጵያ በድርድር የሚመጡ መፍትሔዎችን፣ በአፍሪካ የሚመሩ የሽምግልና ሂደቶችን እና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ለሁሉም ሀገራት በእኩልነት መተግበርን እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የትብብር ስምምነቶች ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ ግልጽ የሥራ ተግባራትና የጊዜ ሰሌዳዎች ያሉት የተግባር ዕቅድ እንዲዘጋጅ ሐሳብ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የመደመር ፍልስፍና እያንዳንዱ አጋር አካል ለጋራ ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እንዳለው እንደሚያምን ጠቅሰው፣ ዕውቀት በሁለት አቅጣጫ መንቀሳቀሱ ለዘላቂ ሽርክና መሠረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: