Search

ኢትዮጵያ የልማት ውሳኔዎቿን ወደ ተግባር ለመቀየር በምግብ፣ በኃይል እና በዕውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረገች ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 48

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ እና የልማት ውሳኔዎቿን ወደ ተግባር ለመቀየር በምግብ፣ በኃይል እና በዕውቀት ላይ ኢንቨስት እያደረገች መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ3ኛው ሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከ100 ዓመት በላይ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል የዘለቀው የወዳጅነት ግንኙነት በጋራ መከባበርና በአንድነት መንፈስ የተገነባ መሆኑን አስታውሰዋል።

በ1896 ከዓድዋ ድል በኋላ የሩሲያ ቀይ መስቀል ተልዕኮ የቆሰሉ ወታደሮችን ለማከም ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን እና የሕክምና መመሪያን ወደ አማርኛ መተርጎሙን ጠቅሰው፣ ይህ ታሪካዊ ተግባር ዕውቀትን ለሰው ሕይወት ማዳን እንዳዋለ ገልጸዋል።

ዛሬም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረጉ ስምምነቶች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች መቀየር እንዳለባቸው አመልክተዋል።

በምግብ ዘርፍ ከሩሲያ ጋር በግብርና ማሽነሪዎችና በምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ላይ በጋራ በመሥራት የግብርና ምርትን ማሳደግና ተጨማሪ እሴት ያለው ምርት ማቅረብ እንደሚቻል ጠቅሰዋል።

ይህም የዜጎችን የምግብ ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል።

በኢንቲሃድ አብራር

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: