Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው ሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ ያደረጉት ንግግር ዋና ዋና ሐሳቦች፡-

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 65

ሦስቱ የኢትዮጵያ የትኩረት መስኮች እና የሩሲያ ትብብር

ምግብና ግብርና፡- የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ዘላቂ የግብርና ኢኮኖሚ ለመገንባት ከሩሲያ ጋር በእርሻ ማሽነሪዎች አቅርቦት እና ምርትን እሴት ጨምረው በሚያቀነባብሩ ኢንዱስትሪዎች መስክ በጋራ መሥራት።

ኢነርጂ እና የኒውክሌር ሳይንስ፡- የዓለም አቀፉን የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) የደኅንነት መስፈርት የጠበቀ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከሩሲያ ጋር ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

እውቀት እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፡- የዳታ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅና በአፍሪካ ቋንቋዎች የሚሠሩ ቴክኖሎጂዎችን ለማበልጸግ አዲስ አበባ ውስጥ የመደመር ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ በመቋቋም ላይ ነው።

ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የፋይናንስ ሥርዓት

የሽርክና ኢንቨስትመንት፡- የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ በመድኃኒት እና በማሽነሪ ምርት ዘርፎች በሽርክና እንዲሰሩ ጋብዘዋል።

የሁለትዮሽ የክፍያ ሥርዓት፡- በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ ቀላልና ወጪ ቆጣቢ የሚያደርግ ቀጥተኛ የክፍያ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት ጠቁመዋል።

ዲፕሎማሲያዊ እና ጂኦ-ፖለቲካዊ መልዕክቶች

በጉባኤው የሚጸድቀው አዲሱ የድርጊት መርሐ ግብር ግልጽ ተግባራትን እና የሚፈጸምበትን የጊዜ ሰሌዳ ያካተተ እንዲሆን ሐሳብ አቅርበዋል።

ቀጣዩን ጉባኤ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የማስተናገድ ፍላጎት አላት።

ኢትዮጵያ በድርድር የሚመጡ ሰላማዊ መፍትሔዎችን፣ በአፍሪካውያን የሚመራ ሽምግልናን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ያለ አድልዎ በሁሉም ሀገራት ላይ በእኩልነትና በወጥነት እንዲተገበር የምትደግፍ መሆኗን ገልጸዋል።

ታሪካዊና የእውቀት ልውውጥ

ከዓድዋ እስከ መደመር፡- በ1888 ዓ.ም ከዓድዋ ጦርነት በኋላ የሩሲያ ቀይ መስቀል ልዑክ የሕክምና መመሪያ መጽሐፍን ወደ አማርኛ መተርጎማቸውን እና ከ130 ዓመታት በኋላ በዚህ ዓመት ደግሞ መደመር መጽሐፍ ወደ ሩሲያ ቋንቋ መተርጎሙን የእውቀትና የአስተሳሰብ ልውውጥ ማደጉን አንስተዋል፡፡

በበረከት ሽመልስ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: