Search

ማንቸስተር ዩናይትድ በቦርንማውዝ 3 ለ 0 ተሸነፈ

እሑድ ጥቅምት 15, 2019 66

በስምንተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኦልድ ትራፎርድ ቦርንማውዝን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 ተሸንፏል።

አምበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተጠባባቂ ሆኖ በጀመረበት ጨዋታ፣ ራያን እና ትራቨርኒየር በመጀመሪያው አጋማሽ እንዲሁም ኢቫኒልሰን በሁለተኛው አጋማሽ የቦርንማውዝን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

ይህ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ በሁሉም ውድድሮች ለስምንተኛ ተከታታይ ጊዜ ነጥብ የጣለበት ሲሆን፣ ከነዛ ስምንት ጨዋታዎች አምስቱን በሽንፈት ነው ያጠናቀቀው።

በሊጉ ለ3ኛ ጊዜ የተሸነፈውና ሦስት ነጥብ ካገኘ 45 ቀናት የተቆጠሩት ማንቸስተር ዩናይትድ ከወራጅ ቀጣናው በሁለት ከፍ ብሎ በሰባት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቦርንማውዝ በዘጠኝ ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: