ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ157 ሀገራት ከቀዳሚ 3 የንግድ አጋሮች ተርታ መመደቧን የቻይና የጉምሩክ አጠቃላይ አስተዳደር ኃላፊ ሱን ሜይጁን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
እ.አ.አ. በ2024 ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ከተሳተፉ ሀገራት ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ 22 ትሪሊየን ዩዋን ወይም 3 ትሪሊየን ዶላር ገደማ ደርሷልም ነው የተባለው።
ከ2021-2025 እየተተገበረ በሚገኘው 14ኛው የአምስት ዓመት እቅድ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ የላቲን አሜሪካ፣ የአፍሪካ እና የመካከለኛው እስያን ጨምሮ ቻይና ከዓለምአቀፍ ገበያዎች ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ ከ10 በመቶ በላይ እድገት መሳየቱም ነው የተገለፀው።
ኃላፌ ቻይና ለዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተው እ.አ.አ ከ2021 ጀምሮ ልማትን ለማሳደግ 519 ዓለም አቀፍ የትብብር ሰነዶችን መፈራረሟን መግለጻቸውን ዥንዋ ዘግቧል።
በሴራን ታደሰ