አሌፋት የግጥም ስብስብ እና ጥቁር ሽታ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ ስራዎቹ የሚታወቀው ደራሲ መሃመድ ነስሩ የተዘጋጀው "አመፀኛ ነፍሶች" የተሰኘው መጽሐፍ ተመረቀ።
የደራሲው ሶስተኛ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ የሆነው መጽሃፉ በብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ባለስልጣን አዳራሽ በተካሄደ ስነ-ስርአት ተመርቋል።
“አመፀኛ ነፍሶች” 18 በተለያዩ ማህበራዊ እና በስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር በ188 ገፆች ያሉት ስራውን ለገበያ ያቀረበው ደራሲ መሃመድ ነስሩ ከመዝናኛ ጋዜጣና መጽሄት እስከ ፍትህ መጽሄት፤ ከአዲስ ነገር ጋዜጣ እስከ አዲስ አድማስ ጋዜጣ “ሶፎኒያስ አቢስ” በተሰኘ የብእር ስሙ ለዓመታት ባሳተማቸው ስራዎቹ ይታወቃል፡፡
ከሐዋሳ ዪኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን በEnvironmental Health Science ያገኘው ደራሲ መሃመድ ነስሩ ጥልቅ ሃሳቦችን ያዘሉ ጽሁፎቹን በዩኒቨርሲቲው ቆይታው “መቅረዝ” በተባለው የኪነ-ጥበብ ቡድን ውስጥ ደማቅ ተሳትፎ ከሚያደርጉና ተወዳጅ ከነበሩ የስነ-ጽሁፍ ሰዎች አንዱ እንደነበር ወዳጆቹ ይናገራሉ፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርአቱ ላይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር)፣የአእምሮ ጤና ሀኪሙ ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ዶ/ር አበባ የሺጥላ፣ ገጣሚ ዳዊት ጸጋዬ የደራሲውንና የራሳቸውን የጥበብ ስራዎች ያቀረቡ ሲሆን መድረኩን ጋዜጠኛ እጸገነት ላቀ መርታዋለች።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: