ሀገራዊ ገጽታን በማጉላት የቱሪዝም እምቅ አቅምን ከፍ ለማድረግ ያለመው “ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ” የቁንጅና እና የቱሪዝም ውድድር አሸናፊውን ለመለየት ከደቂቃዎች በኋላ መካሄድ ይጀምራል።
በማህበራዊ ሚዲያ የተመዘገቡ ከ1 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች በየደረጃው ባደረጓቸው ውድድሮች እንደ ወንጪ ሐይቅ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚያስተዋውቁ ማስታወቂያዎችን እንዲያዘጋጁ ተደርጓል።
ቀጥሎም በሂደቱ የተለዩ 60 የተወዳዳሪዎች በ6 ታሪካዊ መዳረሻዎች ማለትም በጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ ሐረር እና ድሬዳዋ ተዘዋውረው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲያዘጋጁ በማድረግ ለዛሬው የፍጻሜ ውድድር 21 ተወዳዳሪዎች ተመርጠዋል።
የዛሬው የፍጻሜ ውድድር ተፎካካሪዎች በሠሯቸው ቪዲዮዎች፣ ስለዘርፉ ባላቸው ዕውቀት እና በሚቀርቡላቸው የቱሪዝም ጥያቄዎች መሠረት በዳኞች ተገምግመው ነጥብ የሚያዝላቸው ይሆናል።
በዚሁ መሠረት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የውድድሩ አሸናፊ የምትሆነው ተወዳዳሪ የ5 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደምትሆን እና “የኢትዮጵያ የቱሪዝም አምባሳደር” በመሆን ለአንድ ዓመት እንደምታገለግል ተገልጿል።
ይህ ሀገራዊ የቱሪዝም እና የቁንጅና የፍጻሜ ውድድር ኢቢሲ ከደቂቃዎች በኋላ በመዝናኛ ቻናሉ በቀጥታ ማስተላለፍ ይጀምራል።
በሃና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: