የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ቁሩንፉድ ኤቨንትስ በትብብር ያዘጋጁትና የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም አቅም ለማጉላት ያለመው “ጂ ፓወር ፌስ ኦፍ ኢትዮጵያ” የቁንጅና እና የቱሪዝም ውድድር የፍጻሜ ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል።
ከጅምሩ ከ1 ሺህ በላይ ተፎካካሪዎችን ያሳተፈው ፉክክር በርካታ ሂደቶችን አልፎ ዛሬ በስካይላይት ሆቴል በምርጥ 21 መካከል እየተደረገ ላለው የፍጻሜ ውድድር ደርሷል።
በውድድሩ፣ ተፎካካሪዎች በሠሯቸው ቪዲዮዎች እና በሚቀርቡላቸው የቱሪዝም ጥያቄዎች መሠረት በዳኞች ተገምግመው ነጥብ እየተያዘላቸው ነው።
በዚሁ መሠረት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የውድድሩ አሸናፊ የምትሆነው ተወዳዳሪ 5 ሚሊዮን ብር ተሸልማ “የኢትዮጵያ የቱሪዝም አምባሳደር” በመሆን ለአንድ ዓመት የምታገለግል ይሆናል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: