Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር ተወያዩ

ማክሰኞ ኅዳር 01, 2019 83

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር በአዲስ አበባ የከተማ ለውጥና ዘላቂ ልማት ዙሪያ ያለውን ትብብር ለማጠናከር መወያየታቸውን ገለጹ።

ከተማችን በሻንጋይ በተካሄደው የዓለም የከተሞች ቀን ያገኘችውን የዘላቂ የከተሞች ልማት ሽልማትና በሴኡል የተሰጣትን የስማርት ከተማ ዕውቅና በማስመልከት፣ የዩኤን ሃቢታት ዋና ዳይሬክተር እንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸውን ገልጸው፣ እኛም ምስጋናችንን ገልጸናል ብለዋል።

በቀጣይም በከተማ ልማትና ፕላን ያለንን ትብብር በማጠናከር፣ ቀጣዩን የዓለም የከተሞች ቀን በአዲስ አበባ በስኬት ለማክበር በቅንጅት ለመሥራት ተመስማማታቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅሰዋል።

በቅርቡ የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር ለማሸጋገርም የጋራ የትግበራና የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ፕሮጀክቶች በመለየት ላይ መወያየታቸውን አመላክተዋል።

አዲስ አበባ COP32ን ለማስተናገድ በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የUN-Habitat ስትራቴጂያዊና ቴክኒካዊ አጋርነት የከተማችንን የልማት አጀንዳ ለማፋጠንና ዘላቂ ውጤት ለማስገኘት ጠቃሚ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ነው ያሉት።

ዓላማችን አጋርነትን ወደ ተግባር፣ ተግባርን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለሕዝባችን ዘላቂ ጥቅም ማስገኘት ነው ሲሉም አረጋግጠዋል።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: