Search

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኞ ኅዳር 07, 2019 134

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 664 ወንዶች፣ 387 ሴቶች እና 35 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 63 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል።

መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ116 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: