Search

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ ከባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

ማክሰኞ ኅዳር 08, 2019 104

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በመቐለ ከተማ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በውይይቱ ላይ የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

ከዛሬ ኅዳር 8 ቀን ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በመቐለ ከተማ የሚያካሂዱት ልዑካኑ፣ በቆይታቸው ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋርም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይቶቹም የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት፣ የተፈናቃዮች መልሶ መቋቋም፣ የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተን እና መልሶ የማቋቋም (DDR) ሂደት እንዲሁም የክልሉ ዘላቂ ሰላም ጉዳዮች በዋናነት እንደሚነሱ ተመልክቷል።

በአስማረ ብርሃኑ        

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: