የትግራይ ክልል ባለ አደራ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ አሰፋ አብርሃ ትግራይን ለተመድ ልዑካን እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ክልሉ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ እና የሚያስፈልጉ ድጋፎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በጦርነቱ በትግራይ ክልል የተከሰተው የተወሳሰበ ችግር ዓለም አቀፉን የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚፈልግ አንስተዋል።
የጦርነቱ ተጎጂዎች ወደ ቀደመ ሕይወታቸው እየተመለሱ በመሆኑ ለእነሱ ድጋፍ ማድረግ እና ማቋቋሙም ትኩረት እንደሚሻ አብራርተዋል።
የተቋቋመው የባለአደራ አስተዳደር ተቋማትን አገልግሎት የማስጀመር ሥራውን በስኬት እያከናወነ መሆኑን አቶ አሰፋ አብርሃ ገልጸዋል፡፡
የመቐለ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይ ቀናት የአክሱም እና የሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች አገልግሎት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።
ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ሥልጠና ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆኑን እና እነሱን በማሰልጠን ወደ ማኅበረሰቡ የመመለስ ሥራውም በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በጦርነት እና በድርቅ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎችም የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።
በአስማረ ብርሃኑ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: