የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ኤሌና ማርኬዝ የሀገሪቱን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመምራት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጋር አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቷ ቦሌ አየር መንገድ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቷ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮ - ኮሎምቢያ የቢዝነስ ፎረምም በነገው ዕለት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በኤዶም አማረ
#EBCdotstream #ETV #Ethiopia #Colombia