የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካ ህዝቦችን በማቀራረብ አህጉራዊ ገበያን ይፈጥራል ሲል የሀገር አቀፍ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ገለፀ።
በዚህ ዙሪያ ከኢቢሲ አዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ ዝግጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሀገር አቀፍ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አበባየሁ ግርማ፥ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ኢትዮጵያ አምራችነቷ እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በስፋት እየገነባች በመሆኑ ምርቶቿን ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፋ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ላይ መሸጥ እንደምትችልም ነው ያነሱት።
በነጻ የንግድ ቀጣናው አማካኝነት በአፍሪካ ቀዳሚ ለሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተጨማሪ የመንገደኛና የካርጎ አገልግሎት የመስጠት ዕድል እንደሚፈጠርለት ነው የጠቀሱት።
በሜሮን ንብረት
#Trade #AfCFTA #Ethiopian_airlines