ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው የሆስፒታሉ ግንባታ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ አሁን ላይ ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ መድረሱን ገልጸዋል።
ባለ አምስት ወለል የሆነው ይህ ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታው ሲጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት ለኅብረተሰቡ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥ አመላክተዋል።
የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት መንግሥት የሚያደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል መሆኑንም ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: