Search

ኢትዮጵያ ያላትን የቴምር ምርት ለማሳደግ መሰረት የሚጠለው ዓለምአቀፍ ፌስቲቫል

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 123

በፌስቲቫሉ መክፈቻ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ መካሄዱ የኢትዮጵያ እና የተባባሩት አረብ ኢሜሬትስን የኢኮኖሚ ግኑኝነት ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን የቴምር ምርት እንድታሳድግ እና ዓለምአቀፍ ተምክሮ እንድታገኝ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
የግብርና ሚኒስቴር የእርሻ እና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን፤ ፌስቲቫሉ የቴምር ምርትን የኤክስፖርት አቅም ለማሳደግ እና የአግሮ-ኢንዱስትሪ ትስስሮችን ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።
ፌስቲቫሉ ምርጥ ልምዶችን ለመለዋወጥ ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም አንስተዋል።
 
 
በኢትዮጵያ የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ረሺድ አብዱላህ፥ ፌስቲቫሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን የሚያጠናክር በመሆኑ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖሯቸው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የ'ካሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸር ኢኖቬሽን' ሴክሬተሪ ፕሮፌሰር አብዱልዋሃብ አል-ቡካሪ፤ ፌስቲቫሉ ሙያዊ ልውውጦችን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶችን እንደሚያሳድግ ገልፀዋል።
በፌስቲቫሉ የተለያዩ ሀገራት ነጋዴዎች አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካለት ተገኝተዋል። ፌስቲቫሉ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ይቆያል።
 
 
በሁሴን ሙሃመድ