Search

በ2018 በጀት ዓመት 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 106

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ።

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን የበጀት ዓመቱየታክስ ንቅናቄ አካሂዷል።

በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ፤ ግብር ከፋዮች ግብርን ከመሰወር፣ ከማጭበርበር እና ከሕገ ወጥ ግብይቶች ራሳቸውን እንዲቆጥቡ አሳስበዋል።  

የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በማስፋት ክልሉ ያለውን አቅም የሚመጥን ገቢ ለመሰብሰብ ትኩረት እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ አበበ በበኩላቸው፤ በ2017 በጀት ዓመት ክልሉ 4.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 5.86 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደቻለ ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ሰፊ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ለተለያዩ ግብር ከፋዮች እና ባለድርሻ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል።

 

በነስረዲን ሀሚድ