Search

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምድቡን አወቀ

ማክሰኞ ነሐሴ 20, 2017 55

የሴቶች ካፍ ሻምፒንስ ሊግ ማጣሪያ የምድብ ድልድል በግብጽ ካይሮ ይፋ ተደረገ፡፡
ኢትዮጵያን በመወከል በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ ዞን በማጣሪያው የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምድብ ሁለት ላይ ተደልድሏል፡፡
የባለፈው አመት የዞኑ ሻምፒዮን ንግድ ባንክ ከቡሩንዲው ቶፕ ገርል አካዳሚ እና ከሩዋንዳው ራዮን ስፖርት ጋር ተደልድሏል፡፡
ዘጠኝ ቡድኖች በሚሳተፉበት የሴካፋ ዞን የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ምድብ አንድ ላይ የኬንያው ኬንያ ፖሊስ፣ የኤርትራው ደንዲ እና የዩጋንዳው ካምፓላ ፖሊስ ተደልድለዋል፡፡
በምድብ ሶስት ደግሞ የታንዜንያው ጄኬቲ ኩይንስ፣ የደቡብ ሱዳኑ ጆይንት ስታር እና የዛንዚባሩ ጀኬዩ ፕሪንስ ተደልድለዋል፡፡
ውድድሩ ከነሃሴ 9 ጀምሮ እስከ መስከረም 6 በኬንያ ኒያዮ ስቴዲየም የሚደረግ ይሆናል፡፡
 
 
በአንተነህ ሲሳይ