ኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ፍራንሲያ ማርክኬዝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቴውስ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ከፍታለች።
የኤምባሲው መከፈት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብርን ለማጎልበት ትልቅ እርምጃ ነውም መባሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በ1967 በአዲስ አበባ የከፈተች ሲሆን፤ ኤምባሲው ከ1974 ጀምሮ ዝግ ሆኖ ቆይቶ ነበር።
ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ ከ1949 ጀምሮ የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነበራቸው።