የሁል ጊዜ ህልማችን እውን የሚሆነው በየእለቱ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ያለዕረፍት በመስራታችን እና በፈጣሪ እርዳታ ነው ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን-ጎሮ-ቦሌ አየር መንገድ ቪአይፒ ተርሚናል የተገነባው የኮሪደር ልማት የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ለሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአዋቂ የሚሆኑ በርካታ ልማቶችን ማካተቱን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ማንሰራራት የሚያረጋግጡ እና የሚያበስሩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሥራዎቹ ትውልድን የሚያንፁ አንዲሁም መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በቀጣይም ሌሎች ልማት ያልደረሰባቸው የከተማዋን አካባቢዎች ገፅታ የሚቀይሩ ሥራዎችን በማከናወን ከተማዋን ይበልጥ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለነዋሪዎቻችን ሰፊ እና ጽዱ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ አካታች እና ሁሉን ነዋሪ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረድተዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#ebcdotstream #corridor #adisababa