Search

እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣው ሕገ- ወጥ የሰዎች ዝውውር

ቅዳሜ ነሐሴ 24, 2017 56

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በርካቶችን ለኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እና ወንጀል ያጋለጠ ነው።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ የሆኑት ራቢያ በክሩ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ የመለመለ፣ ያጓጓዘ፣ ያስጠለለ እንዲሁም የተቀበለ ከ15 እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪነት ደግሞ ከ150 ሺህ ብር እስከ 500ሺህ ብር የሚደርስ መቀጮ እንደሚደርስበት ያስረዳሉ።

ሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ የአዕምሮ እና የአካል እክል ያለባቸውን ሰዎች ለሕገ-ወጥ ዝውውር መዳረግ እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን ኃላፊነቱን መከታ በማድረግ በወንጀሉ ድርጊት ተሳታፊ የሆነ፤ ድርጊቱ በተጎጂው ቤተሰብ፣ ወላጅ እንዲሁም አሳዳጊ የተፈጸመ ከሆነ ደግሞ ከ25 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣም ተናግረዋል፡፡

ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል መለሰ በበኩላቸው ፤በየክልሎች የተሰማሩ ሕገ-ወጥ ደላሎች የተሻለ ሕይወት ታገኛላቹ በማለት የማታለል ሥራዎችን እንደሚሰሩ ነው ያነሱት፡፡

በሕገ- ወጥ የሰዎችን ዝውውር ምክንያት በየጊዜው እየደረሰ ያለውን ሞት እና እና እንግልት ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ እና አጋር አካላት በጋራ ወንጀሉን ሊከላከሉ ይገባል ብለዋል፡፡

በሜሮን ንብረት

#EBC #Ebcdotstream #Illegal #migration