በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከብራይተን የተጫወተው ማንችስተር ሲቲ 2 ለ 1 ተሸንፏል።
በአሜክስ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ሲቲ እርሊንግ ብሮውት ሃለንድ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ለመሸነፍ ተገዷል።
የ39 አመቱ ጄምስ ሚልነር በፍጹም ቅጣት ምት እና ግሩዳ የብራይተንን የአሸናፊነት ግቦች አስቆጥረዋል።
ሃላንድ በ100ኛ የፕሪሚየር ሊገ ጨዋታው 88ኛ ግቡን ቢያስቆጥርም ክለቡን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም።
640ኛ የፕሪሚር ሊግ ጨዋታውን ያደረገው የ39 ዓመቱ ጄምስ ሚልነር በሊጉ ግብ ያስቆጠረ 2ኛው በእድሜ ትልቁ ተጫዋች ሆኗል።
በ2ኛ ሳምንት በቶተንሀም የተሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በሊጉ በተከታታይ ለመሸነፍ የተገደደበትን ውጤትም አስመዝግቧል።
ዌስትሀም ዩናይትድም በውድድር አመቱ የመጀመርያ ድሉን አስመዝግቧል። ኖቲንግሀም ፎረስትን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአንተነህ ሲሳይ