የያቤሎ አየር ማረፊያ ሥራ መጀመር በርካቶች በአካባቢያችን ያለውን እውነታ እንዲመለከቱ ዕድል ይሰጣል ሲሉ የያቤሎ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
“ያልሞተ ብዙ ያያል” ያሉት ነዋሪዎቹ፤ የቦረና ተወላጅ እና ነዋሪ ለሆነ ሰው ይህን ከማየት በላይ የሚያስደስት ነገር የለም ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ለኢቲቪ ገልፀዋል።
ከዓመታት በፊት በአካባቢያችን ተከስቶ የነበረውን ድርቅ መነሻ በማድረግ ምቹ የዓየር ሁኔታ እንደሌለን እና መሰል ሀሳቦች ቢናፈሱም፤ እውነታው ግን ቦረና ለም፣ ሰላማዊ እና ፍቅር የሆነ ሀገርና ህዝብ መሆኑ ነው ይላሉ ነዋሪዎቹ።
“ህዝባችን እንግዳ ተቀባይ፣ ውሃ ስጡኝ ሲባል ወተት የሚሰጥ ደግ እና ሩህሩህ ህዝብ ነው” ሲሉም ይገልፃሉ።
የገዳ ሥርዓትን ለማጥናት በርካቶች አካባቢው እንደሚጎበኙ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የአየር ማረፊያው መገንባት የጎብኚዎችን ቁጥር እንደሚያሳድገው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
በአፎሚያ ክበበው
#EBCdotstream #ETV #Yabelo #Airport