Search

ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ናት ስንል ከጥንት የነበረ ሀገር በቀል እውቀት አለን ማለት ነው፡ -ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ

ሰኞ ነሐሴ 26, 2017 384

ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት ናት ስንል ከጥንት እየተሸጋገረ የመጣ ሀገር በቀል እውቀት አለን ማለት ነው ሲሉ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ይገልጻሉ፡፡

ምድረ ቀደምት ሀገር፤ የሰው ዘር መገኛ ምድር አለን ስንል ቀደምት ህዝባችን እራሱን ከአካባቢው ጋር ለማላመድ እና ጤናውን ለመጠበቅ ሲጠቀምበት የኖረ እውቀት ነበረው ማለታችን ነው ሲሉ  ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ያስረዳሉ፡፡

ማህበረሰባችን ዘመናዊ ሕክምና ከመምጣቱ በፊት ባሕላዊ ሕክምና ሲጠቀም ቆይቷል የሚሉት ፕሮፌሰሩ በዚህም በርካታ ጠቃሚ እውቀቶች ስለመኖራቸው ነው ለኢቢሲዶትስትሪም የገለጹት፡፡

ለዋቢነትም ከፍ ባሉ ቦታዎች የሚበቅለው በሕክምና ስያሜው  ሀጊኒያ አቢሲኒካበተለምዶ ኮሶ ስለተሰኘው ዕፅዋት አንስተዋል፡፡

የዕፅዋቱ አበባ ተፈጭቶ ሲጠጣ በተለይም ኮሶ ለታየው ሰው እንደሚያሽር አስረድተው፤ በዚህ ዙሪያ ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ ጥናት አካሂደው በማረጋገጣቸው በዓለም አቀፍ መጽሔት ላይ ለህትመት ሊበቃ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

 ሀበርኔራ አቢሲኒካ’ (ድንገተኛ) የፀረ-ተባይ መከላከያ እና ሌሎችም ተጠቃሽ ስለመሆናቸው ፕሮፌሰሩ አክለዋል፡፡

ምናልባትም ሀገር በቀል እውቀቶች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን ብናስቀጥል፣ አሁን ሀገራችን ላይ ከመድኃኒት መሸጫ የምንገዛቸው መድኃኒቶች በኢትዮጵያ ምሁራን የተሰሩ ሊሆኑ ይችል ነበር ነው ያሉት፡፡

የቀደሙ የሀገር በቀል እውቀት የጥናት ግኝቶችን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ምን ተሰርቷል? ሲል ኢቢሲ ዶት ስትሪም ጠይቋል ፡፡

ፕሮፌሰር አፈወርቅ በምላሻቸው ባሕላዊ እውቀቶቻችንን ከዘመናዊው ጋር ማጣመር ላይ ክፍተቶች አሉብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት በአሁኑ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመንግስት እውቅና ተሰጥቶት ስለ ባሕላዊ ህክምና ጥናት ይሰራ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚህም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲፍሎራ ኦፍ ኢትዮጵያበተሰኙ ወደ 13 የሚጠጉ መፅሐፍት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለመድኃኒትነት የሚጠቀሟቸው እፅዋቶች ስለመስፈራቸው አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ማዕከል የአትክልት ሥፍራ በማዘጋጀት የሀገር በቀል እውቀትን መነሻ በማድረግ ወደ 200 የሚጠጉ እፅዋቶችን እየተንከባከብን እና ጥናት እያካሄድን ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪምሙያዬን አጋራለሁ ተመራማሪ ትውልድ አፈራለሁበሚል በክረምት ወቅት ታዳጊዎችን ስለ ሀገር በቀል እውቀት፣ ከበርካታ ዓመታት በፊት ክስተት ስለነበሩ ምሁራኖቻችን እያስተማርን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ያለውን የአቅም ውስንነት በመቅረፍ ግኝቶቻችን ምርት ሆነው በተጨባጭ ተጠቃሚ እንድንሆን ይሰራል ሲሉ ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለዋል፡፡

በአፎሚያ ክበበው

#ebcdotstream #ebc #Ethiopia #FloraofEthiopia #LandofOrigins