Search

በጳጉሜ ቀናት ከፍለው ምርመራ ማድረግ ለማይችሉ ወገኖቻችን ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን - ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል

ማክሰኞ ነሐሴ 27, 2017 79

"ጳጉሜን ለጤና" በሚል በሐኪም ምርመራ ታዞላቸው ከፍለው መመርመር ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል አስታውቋል።

ለኢትዮጵያውን ልዩ በሆኑት የጳጉሜ ቀናት ልዩ የሆነ መልካም ተግባርን ለህብረተሰቡ ለማድረግ ታስቦ የተጀመረ እንቅስቃሴ መሆኑን በማዕከሉ የኢሜጂንግ እና ላቦራቶሪ አስተዳደር ቤተልሄም እንቁብርሃን ገልፀዋል።

ማዕከሉ ይህን በጎ ተግባር ላለፋት15 ዓመታት ማከናወኑን ያስታወሱት አስተዳደሯ፤ በዘንድሮው መርሐ-ግብር በትንሹ 3 ሺህ ገደማ ታካሚዎችን ተደራሽ ለማድረግ ማቀዱን አመላክተዋል።

በዚሁ መሠረት፦

ጳጉሜ 1 - በሁሉም ቅርንጫፎች መስማት ለተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ የጤና ምርመራና ሕክምና የሚደረግ ሲሆን፤ የዓይን ምርመራ እና የመነፅር አቅርቦትም ይኖራል።

ጳጉሜ 2 - በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን መጠለያ የሚኖሩ ወገኖች ለሚገለገሉበት ክሊኒክ የሕክምና መሳሪያዎችን ከማሟላት በተጨማሪ ለነዋሪዎች ሕክምና ይሰጣል።

ጳጉሜ 3 - በሰበታ አካባቢ በሚገኝ የማረሚያ ተቋም ውስጥ ለሚገኙ ታራሚዎች የጤና ምርመራ በማድረግ ሕክምና ከመስጠት ባሻገር ብርድልብስ እና የንፅሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ይበረከትላቸዋል።

ጳጉሜ 4 - በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ሕክምና ማዕከል በዕለቱ የሚታከሙ ህፃናትና ወላጆቻቸው ይጎበኛሉ፤ በማዕከሉ የልብ አልትራሳውንድ ምርመራ እና የሐኪሞች መሰብሰቢያ ክፍሎችም እድሳት ይደረግላቸዋል።

ጳጉሜ 05 - የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ለሚገኙ ነዋሪዎች የበዓል ስጦታዎች ይበረከታሉ።

በአፎሚያ ክበበው 

#EBCdotstream #WDC #Wudase #Pagume #FreeService