የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያወዳድረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የ2017 አሸናፊ የሆነው ወላይታ ድቻ በውሳኔው መሠረት ዋንጫውን በዛሬው ዕለት ተረክቧል።
የወላይታ ድቻ ክለብ አመራሮች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመገኘት ዋንጫውን ከፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የካፍ የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኢሳያስ ጂራ እጅ ተረክበዋል።
በዋንጫ ርክክብ መርሐ-ግብሩ ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር እና የወላይታ ድቻ ክለብ የበላይ ጠባቂ ረ/ኘሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የዞኑ ም/አስተዳዳሪ እና የክለቡ ቦርድ ኘሬዚዳንት አቶ ተስፋሁን ታዲዎስ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ እና የክለቡ ም/ኘሬዚዳንት ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ሌሎች የክለቡ አመራሮች ተገኝተዋል።
#ETV #EBCdotstream #WolaitaDicha #EthiopiaCup