Search

አቅመ ደካሞችን መደገፍ የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ

ረቡዕ ነሐሴ 28, 2017 41

አቅመ ደካማ ዜጎችን መደገፍ የወንድማማችነት እና እህትማማችነት ስሜትን የሚያዳብር የሰው ተኮር እሳቤያችን ማሳያ ነው ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የመውሊድና የዘመን መለወጫ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ከ1 ሺ በላይ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች ማህበራዊ ትስስርን የሚያጎለብቱና የአብሮነት እሴቶች እንዲዳብሩ የሚያስችሉ በመሆናቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የምንታወቅበትን የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህል ይበልጥ በማጎልበት ከአቅመ ደካማ ዜጎች ጎን ልንቆም ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቴዎድሮስ ታደሰ

#ETV #EBCdotstream #Harari #ማዕድማጋራት