የ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል ስናከብር የታላቁ ነብይ መሐመድ (ሰዐወ) በጎ ተግባራትን በመተግበርም ሊሆን ይገባል ሲሉ ኡዝታዝ ቃሲም ሁሴን ተናግረዋል።
የእስልምና እምነት መምህር የሆኑት ኡዝታዝ ቃሲም ሁሴን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ነብዩ መሐመድ ለዓለም እዝነት የተላኩ ነብይ በመሆናቸው ምግባራቸውን መከተል እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ታላቁ ነብይ መቻቻልን߹ መከባበርን߹ የሰው ሐቅ አለመፈለግን አስተምረው አልፈዋል ብለዋል፡፡
ነብዩ መሐመድ የትልቅ ስብዕና ባለቤት እና ለሐይማኖታቸው መስዋትነት የከፈሉ ናቸው ሲሉም ኡዝታዝ ቃሲም ገልጸዋል።
የእርሳቸውን ሐቅ ከመስማት በዘለለም መተግበር እንደሚያስፈልግም ነው የጠቆሙት።
"አላህ እርሳቸውን የላከልን እግር በእግር መልካም ተግባራቸውን እንድንከተል ነው" ሲሉም ኡዝታዝ ቃሲም ሁሴን ተናግረዋል፡፡
በዓሉን ስናከበር በመከባበር እና በመዋደድ እንዲሁም ያለው ለሌለው በመስጠት ሊሆን ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሜሮን ንብረት
#EBC #ebcdotstream #Mawlid