Search

ሐይማኖታዊ መልዕክት የሚተላለፍባቸው መንዙማዎች

ሓሙስ ነሐሴ 29, 2017 31

መንዙማ ምዕመኑን በዜማ በማነቃቃት የሚደመጠውን መልዕክት በሚገባ እንዲሰርጽ የማድረግ ኃይል አለው ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአኪም አህመድ፡፡

የእስልምና ኃይማኖት መምህር የሆኑት ኡስታዝ አብዱልአኪም አህመድ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ መንዙማ ወይም ነሺዳ የሰው ልጅ ትኩረትን ለመሳብ እና ትኩረት ሰጥቶ ይበልጥ እንዲያዳምጥ ያግዛል ሲሉ ያስረዳሉ።

አድማጩም የሚተላለፈውን መልዕክት በጥልቀት እንዲረዳ መንዙማ ትልቅ አቅም እንዳለው ነው ያነሱት።

"መንዙማ ለየት ባለ የዜማ ቅኝት ለነብያችን (ሰዐወ) ያለንን ውዴታ እና ፍቅር ከምንገልፅባቸው መንገዶች አንዱ ነው" ይላሉ።

በመንዙማው የሚካተተው ታሪክ߹ አስተምህሮ እና ሌሎች ሁነቶች የአድማጩን ቀልብ እንደሚገዙም ነው የገለጹት።

አባቶች߹ ወጣቶች ߹ሕፃናት እና ሴቶችም ለየት ባለ ሁኔታ ለነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ያላቸውን ፍቅር በመንዙማዎች እንደሚገልጹም ይጠቁማሉ።

"በእስልምና ውስጥ ምዕመኑን ለማስተማር በሚደረግ ሂደት አድማጮች ነቃ እንዲሉ ለማስቻል በመንዙማ ወይም በነሺዳ መልክ የሚቀርቡ መልዕክቶች መኖራቸውንም ኡስታዝ አብዱልአኪም አህመድ ይገልጻሉ።


በሜሮን ንብረት

#EBC #ebcdotstream #Mewlid