ወይዘሮ አሰለፈች ፀጋዬ ይባላሉ። ነዋሪነታቸው በሻሸመኔ አራዳ ክፍለ ከተማ መናኸሪያ አካባቢ በልዩ ስሙ ቡና ተራ በሚባለው ሰፈር ነው።
ወይዘሮ አሰለፈች በዚህ ሰፈር የወዳደቁ ፌስታሎችን ሰብስበው በመሸጥ እንደዚሁም ከሰል በመቸርቸር ሕይወታቸውን ይመራሉ።
ወይዘሮ አሰለፈች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ደጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ገድባ እንድታጠናቅቅ በውስጣቸው ከነበረው ቁጭት እና ጉጉት የተነሳ ባለፉት 14 ዓመታት በቦንድ ግዢና በድጋፍ መልክ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ማበርከታቸውን ይናገራሉ።
አሁን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመዘጋጀቱ ደስታዬ ወደር የለውም፤ እንኳን ደስ አለን ሲሉም ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለፍፃሜ እንዲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጫወቱት የላቀ ሚናም ወይዘሮ አሰለፈች አመስግነዋል።
አሁን ምኞቴ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት ጉባ ሄጄ ምረቃውን መታደም ነው ብለዋል።
በፈቃደአብ አለማየሁ
#EBCdotstream #ETV #GERD #RenaissanceDam #ሕዳሴግድብ #Inauguration