Search

ኢትዮ-ቴሌኮም "የነገ ተስፋዎች" በሚል መርሐ ግብር ለ80 ሺህ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ

ዓርብ ነሐሴ 30, 2017 57

ኢትዮ-ቴሌኮም በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች  ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር እና ለበጎ አድራጎት ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

"ለነገ ተስፋዎች " የሚል መርሐ ግብር በመቅረፅ በየዓመቱ የተለዩ ድጋፎች በማድረግ ላይ የሚገኘው ኢትዮ-ቴሌኮም፤ በዚህ ዓመትም አነስተኛ ገቢ ላላቸው ማኅበረሰብ ክፍሎች  የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።

2018 . የትምህርት ዘመንም በሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅኖች ለሚገኙ  አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ  80 ሺህ ተማሪዎች 98.8 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ድጋፍ ተደርጓል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ባሻገር "በጎነት "በሚል መርሐ ግብሩ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ 39 የበጎ አድራጎት ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

መርሐ ግብሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሙዳይ የበጎ አድራጎት ማኅበር ውስጥ አስጀምረዋል።

ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበርም ተቋሙ  2.6 ሚሊዮን ብር ገደማ ድጋፍ አደርጓል።

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞችም "በጎነት ለሰብዓዊነት " በሚል መርሐ ግብር  ከደም ባንክ ጋር በመተባበር ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ 19 ቦታዎች የደም ልገሳ መርሐ ግብርም አድርገዋል።

በኤዶሚያስ ንጉሴ