Search

“ቶኪ ቤዓ” በዓል መተሳሰብን ለማዳበር የላቀ ድርሻ አለው - ርዕሰ መስተደድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

ዓርብ ነሐሴ 30, 2017 37

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ "ቶኪ ቤዓ" በዓል በዜጎች ዘንድ መተሳሰብን ለማዳበር እና ሰላምን ለማፅናት የላቀ ድርሻ አለው ሲሉ ተናግረዋል።
የበዓሉ አከባበር አካል የሆነው የፖናል ውይይት በታርጫ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የበዓሉን ባህላዊ ይዘት ይበልጥ ለመጠበቅ እና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጁ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ምክክር ተደርጓል።
በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ ሕብረተሰቡ ለዘመናት ያዳበራቸው ባህላዊ እሴቶች ለትውልድ እንዲተላለፉ በተገቢው መንገድ ሊጠኑ እና ሊጠበቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
 
 
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፤ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የዘመን መለወጫ በዓሉን በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፖናሉ ተሳታፊዎችም ወጣቱ ትውልድ ባህል እና ወጉን ተንከባክቦ በሂደቱም ተጠቃሚ ለመሆን ሊተጋ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተለያዩ ዘርፎች ለዞኑ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደራሲያን እና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ሽልማት አበርክተዋል።
በሰለሞን ባረና