Search

ለሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው የኪነ-ጥበብ ዘርፉ

ዓርብ ነሐሴ 30, 2017 29

የኪነ-ጥበብ ዘርፉ ዘመን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ሲሉ አርቲስት ሙሉ ገበየሁ ያወሳሉ።
ዘመን አይሽሬ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን በቀጣይነት መጠቀም እንደሚገባም ነው አርቱስቱ ያመላከቱት።
ሁለገብ አርቲስት የሆኑት ሙሉ ገበየሁ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የሕዳሴ ግድብ ውጤት እንዲያመጣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችም የነበራቸው ቁርጠኝነት የሚደንቅ ነበር ብለዋል።
ግድቡ ሲጀመር አንስቶ ማኅበረሰቡን በኪነ-ጥበብ በማነሳሳት እና ድጋፍ እንዲያደርግ በማስቻል በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ነው ያስታወሱት።
በርካታ አርቲስቶች ለግድቡ ሥራ በመሳተፍ እና ድጋፍ በማድረግ የበኩላቸው መወጣታቸውን አንስተው፤ ይህ አስተዋጽኦ አሁንም መቀጠል እንዳለበት ነው የጠቆሙት።
በመሆኑም ትውልድ የሚያወሳቸውን የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በማዘጋጀት በቀጣይ የልማት ሥራዎች ላይም መጠቀም እንደሚገባም ነው አርቲስት ሙሉ ገበየው የገለጹት።
 
በሜሮን ንብረት