የኅብር ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ "ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ይገኛል።
የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የበርካታ ባህሎች እና ትውፊቶች ሀገር ናት፤ ይህንኑ ብዝሃነት በአንድነት እና በመተባበር ስሜት ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ሕብረት የተገኘ ድል ነው ያሉት አቶ መለሰ፤ በቀጣይም በኅብር ላይ በተመሰረተ አካሄድ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ገንብተን ማጠናቀቅ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።
ለዚህም የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
በመርሀ-ግብሩ በብዝሃነት እና አንድነት ላይ ያተከረ ሰነድ ቀርቦ በበዓሉ ታዳሚዎች ውይይት ተደርጎበታል።
በጀማል አህመድ