Search

የኅብር ቀን፣ የአዲስ ዓመት እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ስኬት በዓል በኬንያ

እሑድ ጳጉሜን 02, 2017 65

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኅብር ቀንን፣ አዲስ ዓመትን እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት በዓል ተከብሯል።

ዲፕሎማቶች፣ ሚሲዮኖች፣ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ ማኅበራት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ በኬንያ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

ኢትዮጵያ  የራሷ የዘመን አቆጣጠር  ያላት የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤት መሆኗ ሀገሪቱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎቿን በራሷ እንደምትመራ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል::

ኢትዮጵያ የይቻላል መንፈስን የተጎናፀፈችበት ስኬት የዚህ ትውልድ አርበኝነት መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር  ደመቀ አጥናፉ ገልፀዋል::

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያውያን በኅብር ሆነው አይችሉም ስሜትን የሰበሩበት የመደመር ትውልድ ስኬት ሆኗል ሲሉ አንስተዋል።

 

በኤልሻዳይ ወንድማገኝ 

#EBC #ebcdotstream #Unity #ኅብር