Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አካሄዱ

እሑድ ጳጉሜን 02, 2017 66

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ500 ሺ ዜጎች ማዕድ አጋርተዋል።
ማዕዱ የተጋራው ለአቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የመንግሥት ሰራተኞች ነው።
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማዕድ ማጋራት መደጋገፍን፣ አንድነትን እና መተሳሰብን የሚያጎላ መልካም ባህል ነው ብለዋል።
ድጋፉ የተደረገው በከተማዋ የሚገኙ ባለሃብቶችን እና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር መሆኑንም ከንቲባዋ የተናገሩ ሲሆን፤ ከተማ አስተዳደሩም ይህን መልካም እሴት ለማስቀጠል በትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።
 
በክረምቱ ወራትም ምንም ጧሪ፣ ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካምችን፤ የአገር ባለውለታዎችን እና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ 156 ሺህ ያህል የኅብረተስብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች በበኩላቸው ድጋፉ “በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ጠቁመው፤ ለተደረገላቸው ድጋፍም ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል።
በብሩክታዊት አስራት