Search

ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

እሑድ ጳጉሜን 02, 2017 108

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ ውጤት ይፋ ተደርጓል።
የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሥራ አስፈፃሚ አባላትንም የምርጫው አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።
ምርጫውን አካታች ለማድረግ በመሰራቱ ከዑለማ ባሻገር ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የዲያስፓራ ማኅረሰብ አባላት በየዘርፋቸው ወኪሎቻቸውን መምረጣቸው ተገልጿል።
የተመረጡ የሥራ አስፈጻሚ አባላት በታላቁ አንዋር መስጅድ ቃለመሃላ መፈጸማቸው ተጠቁሟል፡፡
ቃለ መሐላውን የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አማካኝነት ተከናውኗል።
በዚህም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፤ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን፤ ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ጁነይድ ሃምዛ እና በተመሳሳይ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሼህ ሐሚድ ሙሣ ሆነው በመመረጣቸው ቃለ መሐላ ገብተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ጠቅላላ ጉባዔ 195 አባላት እንዳሉት ተመላክቷል።
 
በሃብታሙ ተክለስላሴ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: