ኢትዮጵያ በሩስያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው “11ኛው ዓለም አቀፍ ዩናይትድ ካልቸር ፎረም” ላይ እየተሳተፈች ነው።
የባህል ፎረሙ ላይ የተለያዩ ሀገራት የየራሳቸዉን ባህልና እሴት ማስተዋወቅ ችለዋል።
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ያሏት ሀገር እንደሆነች እና በተፈጥሮ ፀጋ የታደለች መሆኗን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ፎረም ላይ ስትሳተፍ በቀጣይ ለዓለም አቀፍ ዘርፈ ብዙ ትብብሮች መሰረት የሚጥሉ ግንኙነቶችን መመስረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ማድረጓንም አስገንዝበዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ፎረሙ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሆኑት አምባሳደር ነብዩ ተድላ በበኩላቸው፤ ተመሳሳይ የባህል ፎረሞች ላይ መሳተፉ በሀገራት መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና የባህል ትስስሮችን ለማጠናከር ዓይነተኛ ሚና እንዳለዉ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
የባህል ፎረሙ ለቀጣይ ሶስት ቀናት መካሔዱን ይቀጥላል፡፡
በፍሬው በኩረፅዮን