ኪን ኢትዮጵያ የባህል እና የጥበብ መድረክ በሩሲያ የመጀመሪያውን የጥበብ ድግስ እያቀረበ ነው፡፡
የባህል ቡድኑ የጥበብ ድግሱን እየቀረበ የሚገኘዉ የባህል ማዕከል በመባል በሚታወቀዉ በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኘው ጥንታዊው አሌክሳንድርስኪይ ቴአትር ቤት ነዉ፡፡
በዚህ የመድረክ ትዕይንት የኢትዮጵያን ሕብረ-ብሔራዊነት የሚያንፀባርቁ ሥራዎች እየቀረቡ ይገኛል፡፡

የባህል እና የጥበብ ቡድኑ የመጀመሪያውን የሩሲያ ዝግጅቱን እያቀረበ ያለው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ65 በላይ ሀገራት ተሳታፊ በሆኑበት የዓለም አቀፍ የባህል ፎረም እየተካሄደባት በምትገኘው ከተማ ላይ ነው፡፡
ይህም የኢትዮጵያን እምቅ የብዝኃ ባህሎችን እና የኪነ ጥበብ ሃብቶችን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያን የባህል ጉዞ በዋናነት የሚያስተባብሩት የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር ነው፡፡
በፍሬው በኩረፅዮን