Search

የሕዳሴ ግድብን የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

ቅዳሜ መስከረም 03, 2018 60

"ኢትዮጵያ ትችላለች" በሚል መሪ ሃሳብ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በዐድዋ ድል መታሰቢያ ተከፈተ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መጠናቀቅ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዘጋጀው አውደ ርዕይ ለእይታ ክፍት በሆነበት ስነ-ስርዓት ላይ በተለያዩ ባለሙያዎች የተሰሩ የስዕል እና የፎቶ ግራፍ ጥበቦች ለዕይታ በቅተዋል።
በፎቶ እና በስዕል አውደ ርዕዩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል እና የከተማ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችም በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ታድመዋል።