Search

የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ከዳር ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው - ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር)

ሰኞ መስከረም 19, 2018 41

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የባሕር በር ጥያቄውን ከዳር ለማድረስ የተጀመሩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ነው የገለፁት።
ኢትዮጵያ የባህር በር ከሌላቸው ሀገራት መካከል ትልቁን የሕዝብ ብዛት የያዘች ሃገር መሆኗን ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
 
በታሪክ የባህር በር የነበረን ቢሆንም በተፈፀመው ደባ ምክንያት የባህር በር ባለቤትነታችን ተነስቶ አሁን ላይ ከቀይ ባህር በቅርብ ርቀት ላይ እንገኛለን ይላሉ።
በመሆኑም ኢትዮጵያ ቀድማ ወደምትታወቅበት የባህር በር ባለቤትነት እንድትመለስ እና ኢኮኖሚዋን እንድታጠናክር ጥረቶች መቀጠል እንዳለባቸውም ነው ያመላከቱት።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ፍትሐዊ እና በርካቶች የሚደግፉት በመሆኑ የዲፕሎማሲ ሥራውን ይበልጥ አጎልብቶ መሄድ እንደሚጠይቅም ነው ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) የገለፁት።