የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ቢዝነስ አመራር ምሁር የሆኑት ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ብሔራዊ ጥቅምን አጉልቶ እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡
ብሔራዊ ጥቅም ሲባል አንድ ሀገር ከሌሎች ሀገራት ጋር በሚኖራት ግንኙነት የማትደራደርበት ጉዳዮችን ለመግለፅ የሚውል ሀሳብ መሆኑን ምሁሩ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ ረገድ የመደመር መንግሥት እሳቤ ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ስትከተላቸው የነበሩ ስርዓቶችን በአግባቡ የፈተሸ እንደሆነም ነው የገለፁት፡፡
መጽሐፉ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ረገድም ጥሩ የፖለቲካ ሰነድ የያዘ ስለመሆኑ ነው የጠቀሱት፡፡
መንግሥት መር የሆነውን እና የነጻ ገበያ ኢኮኖሚን በመፈተሽ የተሻለ የትብብር ኢኮኖሚ ይዞ የቀረበ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡
የወረስናቸው የፖለቲካ እሳቤዎች ምክንያታዊነት የጎደላቸው መሆናቸውን የገለፁት ብሩክ ከድር (ዶ/ር)፤ በመደመር መንግሥት እሳቤ ሀገራችን የሚገባትን የክብር ከፍታ እንድታገኝ በአንድነት መቆም እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እንደሚያነሳም ነው የገለጹት፡፡
አንድ ሀገር ጠንካራ የሚሆነው ጠንካራ ተቋም ሲኖረው ነው ያሉት ምሁሩ፤ የመደመር መንግሥት መጽሐፍም በዚህ ላይ ሰፊ ትንተና እንደሚሰጥና ጉዳዩን አጉልቶ እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡
የመደመር መንግሥት በፖለቲካ ረገድ ትልቅ መፍትሄ ይዞ የመጣ የፖለቲካ እሳቤና ሰነድ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡
በሜሮን ንብረት
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #yemedemermengist #National_Interest