መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣራ ስር በማጣመር እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
ህብረተሰቡ ያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት የተቋቋመው አገልግሎቱ የተገልጋይን ጊዜ ለመቆጠብ እና እንግልቱን ለመቀነስ ስለማስቻሉ ይነገራል።

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ አገልግሎቱ 13 የከተማ አስተዳደር እና 3 የፌደራል ተቋማት እንዲሁም 2 ባኮች፣ በድምሩ 18 ተቋማትን የተጣመሩበት መሆኑን ገልጸዋል።
በማዕከሉ የፋይናንስ፣ ገቢዎች፣ ቤቶች ልማት፣ ትራንፖርት እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ ተቋማት እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ በቀጣይ የሚጨመሩ ሌሎች ተቋማት እንደሚኖሩ ነው የተናገሩት።
ማዕከሉ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸው፤ ይህም የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚያቀላጥፈው እና እንደሚያዘምነው ይጠበቃል ብለዋል።

በሜሮን ንብረት
#EBCdotstream #ETV #MesobCenter #AddisMESOB #A-MESOB