Search

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 67

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የግሸን ደብረ ከርቤ (ግሽን ማርያም) ዓመታዊ የንግስ በዓል በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
በክብረ በዓሉ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር አባ ለይኩን፣ የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መምህር አባ ብስራተ ገብርኤል፣ ሌሎች የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ምዕመናን በግሸን አምባ ታድመዋል።
በየዓመቱ መስከረም 21 ቀን በሚከበረው በዚህ ዓመታዊ የንግስ በዓል ላይ ከመላው ኢትዮጵያ እና ከተለያዩ ሀገራት በርካታ ምዕመናን ይታደማሉ፡፡
በጌትነት ተስፋማርያም