በመዲናዋ አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጤናማ፣ ፅዱ፣ ውብ እና ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ዘርፈ ብዙ መሰረተ ልማቶች ተከናውነዋል፤ በመከናወን ላይም ይገኛሉ።
የመንገድ፣ አረንጓዴና የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች: አንፊዎችና ፕላዛዎች፣ የብስክሌት-መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻ፣ ተርሚናሎች እና የመኪና ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የህዝብ መፅዳጃ ቦታዎች እና የወንዝ ዳር ልማቶች ወዘተ...ተጠቃሽ ናቸው።
ከመሰረተ ልማቱ ጎን-ለጎን ከ5000 በላይ ሱቆች እና ሞሎች ተሰርተው የከተማው ማህበረስብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ከ170 ሺህ በላይ ሰዎች በግንባታ ሂደት የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። አሁንም በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በቀጥታ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል።
በሌላ መልኩም፥ የተለያዩ የውጭና የውስጥ ኢንቨስተሮችን ያሳተፈ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመትንት ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ለአብነትም በ2017 በጀት ዓመት በግልና መንግስት የትብብር አጋርነት ስምምነት 1.56 ትሪሊዮን ብር ካፒታል በጀት በመመደብ 4168 ባለሀብቶች ፈቃድ ያገኙበት ግዙፍ ኢንቨስትመንት እየተከናወነ ይገኛል።