Search

ከተሞችን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 21, 2018 37

የከተማ ማዕከሎቻችንን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ዛሬ የተመለከትናት ጅግጅጋ ባለፈው ጥር ከተመለከትናት ይዞታዋ በሚታይ መልክ የተቀየረች ናት ብለዋል።

በመላው ከተማዋ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤  የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢ የመኖሪያ ሁኔታን በግልጽ እያሻሻሉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

የከተማ ማዕከሎቻችንን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል።

ርዕያችን እንደኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ ጠቃሚ በሆኑልን ጉዳዮች ላይ የተተከለ መሆኑን ማስታወስ ይገባናል ሲሉም አመልክተዋል።

በዚህ መንፈስ የሶማሌ ክልል በቱሪዝም አዳዲስ እድሎችን እየከፈተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ወደመጠናቀቂያ ምዕራፍ የደረሰው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል አዲስ ዋጋ የጨመረ እድል እየፈጠረ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

በአጠቃላይም የተመለከቱት የሥራ እድገት በጅግጅጋ እና በመላው ክልሉ የሚስተዋለውን መነቃቃት የሚገልጽ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #AbiyAhmedAli #Jijiga